RSS

Author Archives: Kassahun Alemu

About Kassahun Alemu

ጦማሪው ዋና የሚያተኩርበት የዕውቀት ክፍል ፍልስፍና በተለይም ሥነ አመክንዮ ክፍል ሲሆን የኢትዮጵያውያንን የጥንት ፍልስፍናዊ አስተምህሮ በሚመለከት የጥናት ዕቅድና ዝግጅት አለው፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ ለዓለም ሁሉ ሥልጣኔዎች መሠረት ነው ብሎ ያምናል፡፡ በሃይማኖት ዙሪያም የራሱ የሆነ ጥቅል ግንዛቤ አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝና ተከታይ ነው፡፡ በትምህርት ደረጃ በኢኮኖሚክስ እና በፍልስፍና ትምህርቶች እስከ ኹለተኛ ዲግሪ ዘልቋል፡፡ በትርፍ ጊዜው የክርክር ጽሑፎችን፣ የተለያዩ መጣፎችንና ግጥሞችን ይጽፋል፡፡ በዚህ ዙሪያም ከአሁን በፊት ‹መሠረታዊ ሎጅክና ሕጸጽ›፣ ‹ብዕረ ገሞራ›(ግጥም)፣ ‹ሀልዎተ እግዚአብሔር› እና 'ቅኔ-ዘፍልሱፍ' የሚሉ መጽሐፎችን አዘጋጅቶ ለአንባብያን አቅርቧል፡፡ ለወደፊትም ለኅትመት ያዘጋጀቸውና ለማዘጋጀት ያሰባቸው ሥራዎች አሉት፡፡ ይህችን መጦመሪያም ያሉትን አሳቦች ለማንሸራሸሪያነት ከፍቷል፡፡

‹ቅኔ-ዘፍልሱፍ› መጽሐፍ ምን ይዞ መጣ? ምንስ ይጎድለዋል?

ከጥበብ ፈለቀ

ብሎብኝ ፍልስፍና ነክ የሆኑ መጽሐፎች ለማንበብ ይማርኩኛል፡፡ ለዚህ በጋዜጣ፣ በመጽሔት፣ ማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በመተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች በፍልስፍና ዙሪያ የሚሠጡ አስተያየቶችን ቀድሜ ለመመልከት ጉጉት ያድርብኛል፡፡ ሰሞኑንም ‹ቅኔ-ዘፍልሱፍ› የሚል መጽሐፍ ገዝቼ አነበብኩ፤ በእውነቱ ጥሩ መጽሐፍ ነው፡፡

ከጸሐፊ ጋር በፌስቡክ የማኅበራዊ ሚዴያ ጓደኛሞች ስለሆንን የሚጽፋቸውን መጣጥፎች እመለከታለሁ፡፡ በተለይም ፍልስፍናን ከኢትዮጵያውያን ጥንታዊ ጥበባት ጋር ለማያያዝ የሚያደርጋቸው ጥረቶች ያስደስቱኛል፡፡ ስለሆነም ‹ቅኔ-ዘፍልሱፍ› የሚል መጽሐፉም ለእኔ ብዙ የተማርኩበትና የተለዩ ሐሳቦችን የያዘ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ በመጽሐፉ ላይ የለኝን ትዝብትና ትችት ጨምሬ አስተያየት ለመስጠት የፈለኩትም ለዚያ ነው፡፡ ሆኖም ወደመተቸቱ ያደላሁም ይመስለኛል፤ ለማንኛውም መልካም ምንባብ፡፡IMG_20171028_185337 Read the rest of this entry »

Advertisements
 

Jokes: Existential Comics

title
theMonument1

theMonument2 Read the rest of this entry »

 

Funny and Smart Logic

Logic: René Descartes

René Descartes is sitting in a bar, having a drink. The bartender asks him if he would like another. “I think not,” he says and vanishes in a puff of logic.

Logic: Jean-Paul Sartre

Jean-Paul Sartre is sitting at a French cafe, revising his draft of ‘Being and Nothingness’.
He says to the waitress, “I’d like a cup of coffee, please, with no cream.”
The waitress replies, “I’m sorry, monsieur, but we’re out of cream. How about with no milk?” Read the rest of this entry »

 

የቅኔና የፍልስፍና ፉክክር (፭)፡- ቅዱስ አውጉስጢን

በካሣሁን ዓለሙ

መግቢያ

ቅኔ ከፍልስፍና ጋር ባለው ጉንኙት ዙሪያ የምናደርገውን ምርመራ በግሪክ ፈላስፎች ዙሪያ ተሸከርክረን፣ ባለፈው ሣምንት የአርስቶትልን ክርከር ዐይተን ነበር ያቆምነው፤ ለዛሬው ቅዱስ አውጉስጢን (St. Augustine) ዕይታ እንቃኛለን፡፡

ቅ.አውጉስጢን የተወለደውና የተማረው በሰሜን አፍሪቃ ነው፤ የኖረበት ዘመን እ.ኤ.አ ከ354- 430 ዓ.ም ነው፡፡ ክርስቲያን ሳይኾን በፊት በሚላን እና በካርቴጅ አስተማሪ እና የት/ቤቶቹ ቀዳሚ ሊቀመንብር ነበር፤ ክርስትናን ከተቀበለ በኋላ ግን ወደ ሰሜን አፍሪቃ ተመልሶ የመኖኮሳት ማኅበርን መሠረተ፡፡ ከዚያም ክህነት ተቀብሎ በሂጶ ጳጳስ ኾነ፡፡ ቅ. አውጉስጢን በተለየ የሚታወቅበት ሥራው የእግዚአብሔር መናገሻ (The City of God) በሚለው መጽሐፉ ነው፡፡

ሊቁ አውጉስጢን ቀድሞ ባለቅኔ ነበር፤ እንዳውም በቅኔው ተወዳድሮ በማሸነፍ እሰከ መሸለም ደርሶ እነደነበር ይነገራል፤ ኋላ ግን ክርስቲያን ሲኾን ያ ኹሉ መውደስ ለባድዕድ አምልኮ የሚቀርብ መኾኑን ተረዳ፡፡ ስለዚህ ቅኔን ገሸሽ በማድረግ ወደ ማራከስ ዞረ፤ ፍልስፍናንም የክርስትና ሃይማኖት ገረድ አድርጎ በመቅጠር፣ የፕሌቶ የቅኔና የፍልስፍና ንትርክ ቀይሮ በቅኔና በሃይማኖት መካከል የሚደረግ ‹የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ›  ፉክክር አድርጎ ሞገተ፡፡

NT; (c) Kingston Lacy; Supplied by The Public Catalogue Foundation Read the rest of this entry »

 
 

የቅኔና የፍልስፍና ፍክክር (፬)፡- ሊቁ አርስቶትል

በካሣሁን ዓለሙ

ባለፈው ከግሪክ ፈላስፎች መካከል የሶቅራጥስና የፕሌቶን የቅኔ ዕይታ ተመልክተናል፤ በዛሬ መጣጥፌ ከአርስቶትል እስከ አውጉስጢን ያለውን የቅኔ ዕይታ ለማቅረብ ቃል ብገባም ሊቁ አርስቶትል ነገር አስረዝሞ አለቀኝ ስላለ የእሱን ዕይታ ብቻ ለማቅረብ ተገድጃለሁ፡፡፡

ከፕሌቶ ያላነሰ በአውሮጳ አስተምህሮ ተፅዕኖ ፈጣሪ የኾነው ተማሪው አርስቶትል በቅኔና በፍልስፍና

አታካራ ላይ ያለው ተፅእኖ በመምህሩ ቦይ ውስጥ የሚፈስ ቢኾንም ለቅኔ በሰጠው ደራጃ፣ ዋጋ እና መነሻ ይለያል፡፡ ቅኔን የሚመዝነው በሚሠጠው ጥቅምና ባለው ዋጋ ሲኾን እንደ ፍልስፍና የሚመሠረተው በመደነቅ ላይ መኾኑን ይስማማል፤ ደረጃ ሲሰጥም ቅኔን የታሪክ ታላቅ ወንድም፣ የፍልስፍና ተከታይ አድርጎ ነው፡፡
aristotle

Read the rest of this entry »

 

የቅኔና የፍልስፍና ፉክክር 3፡- በሶቅራጥስና በፕላቶ ዕይታ

በካሣሁን ዓለሙ


ባለፈው መጣጥፍ የቅኔ ጥበብ ጥንታዊነትንና አጠቃላይ በፈላስፎች ያለው ዕይታ በዘመናት ምን ይዘት እንዳለው ተመልክተናል፤ በዚህኛው መጣጥፍ ደግሞ ከፍልሱፋኑ የኹለቱን የሶቅራጥስንና የፕላቶ ተፅእኖ ይዘት ለማየት እንሞክራለን፡፡

የዓለማችን የፍልስፍና ካርታ የተሠራው በሶቅራጥስ ቀያሽነት፣ በፕላቶ ንድፍ አውጭነት እና በአርስቶትል ‹የሁሉን በየፈርጁ› ድምበር ሠሪነት ነው፤ እነዚህ ሥሉስ ሊቃውንት በተጠበቡበት ካርታም የዓለም ጠቢባን አአምሯቸው ዞሯል፤ እስካሁንም የተደረገው ማሻሻል እንጂ የካርታው ንድፍ አልተለወጠም፡፡ ከሦስቱ መካከልም የሶቅራጥስና ፕላቶ ፍልስፍና ለያይቶ ማስቀመጥ ትንሽ ያስቸግራል፤ ምክንያቱም ፕላቶ የሶቅራጥስ ጸሐፌ ትዛዝ የነበረ ሲኾን ሶቅራጥስ ደግሞ  ለፕላቶ አፈቀላጤው ነበርና፡፡index Read the rest of this entry »

 

የቅኔና የፍልስፍና ፉክክር (፪)

ካሣሁን ዓለሙ

ባለፈው ቅኔና ፍልስፍና በመደነቅ መሠረታቸው እና የተፈጥሮን (የእውነትን) ምሥጢር ለመግለጥ በመጣራቸው አንድነት ቢኖራቸውም በስልታቸው ቅኔ ሰምና ወርቅን (ኅብርነትን)፣ ፍልስፍና ደግሞ አመክንዮን (ምክንያታዊነትን) በመመርመሪያነት ስለሚወስዱ መለያየታቸውን፤ ኹለቱም ግን የተፈጥሮን ቅንብር የሚያመጠኑ መሠረታዊያን ጥበባት መኾናቸውን፣ ተመልክተን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የቅኔን ጥንታዊ ጥበብነት እና ከሶቅራጥስ ጀምሮ በምዕራባዊያን ፈላስፎች ዘንድ ያለውን የዕይታ ኹኔታ በጥቅሉ ለማየት እንሞክራል፡፡

  1. ቅኔ ጥበብ ጥንታዊነት

የቅኔና የፍልስፍናን ታሪካዊ ዳራ ስንፈትሽ የፍልስፍና ውልደት ሳይበሠርና የሰው ልጅ ዕውቀት በትምህርት ሥረዓት ዘርፍ (ቅርንጫፍ) ሳይከፋፈል በፊት ቅኔ በብቸኝነት ኹሉንም ትምህርት በአንድነት አምቆና ከተፈጥሮ ኅብርነት ጋር ተናቦ (አናቦ) የሚገኝ ጥበብ ነበር፤ ተመራማሪዎቹም ይኽ የዚኽኛው የትምህርት ዓይነት ነው፤ ያኛው ከዚያኛው ጋር ይያያዛል/ይለያል በማለት አይከፋፍሉም ነበር፡- ከአርስጣጣሊስ (አርስቶትል) ጀምሮ ነው ዕውቀት በክፍል በክፍል እየተመደበ ድንበር የተበጀለት፡፡ በጥንት ዘመን የአብዛኞቹ ጠቢባን የምርምር ማዕከልም ከተጻፈ ላይ መፈለግ ሳይኾን የተፈጥሮን ህላዌ እና የፍጥረታትን መስተጋብራር ማስተዋልና መመርመር ነበር፡፡ ይኽንን ነው የሰው ልጅ በፊደላት ቀርጾ፣ በዚያም ወደ ጽሑፍ ገልብጦ ተወራራሽ ጥበብ ያደረገው፡፡ ተፈጥሮ ደግሞ በኅብርነት፣ በዕምቅነት፣ በዜማ… ቅኔ የተሠራች መኾነዋን ትመሠክራለች፤ ምስክርነቷን ያስተዋለና በአግባቡ ያዳመጠ ባለቅኔ ይኾናል፡፡ ስለኾነም በየትኛውም ሥፍራ ቢኾን በጥንት ጊዜ  የሰው ልጅ የዕውቀቱ መሠረት ቅኔ ነበረ፡፡ Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: