RSS

Monthly Archives: January 2018

ትኩርት ያላገኘው ባህላዊ የተጠየቅ ልጠየቅ ክርክር ጥበብ

በካሣሁን ዓለሙ

(ይህ ጽሑፍ በውይይት መጽሔጽ ቁ.19 ታትሞ የወጣ ነው)

  1. መንርደሪያ

እኛ ኢትዮጵያዊያን በባህላችን የሚደነቁ ጥበባትን በተለይም የዳበረ የራሳችን ባህላዊ (ልማዳዊ) የትችትና የክርክር ባህል ያለን ሕዝቦች ብንኾንም በተለያየ ማኅበረሰቦች የዳበሩት የባህላችን ማሳያዎች ተጠንተውና ተገናዝበው ለዘመናዊ ትምህርትና ፍትሕ ግብዓት እንዲኾኑ ፍልስፍናቸውና ሥነ አመክንዮአዊ ጥበባቸው አልተመረመረም፡፡

ምንም እንኳን በብዙ የሀገራችን ክፍሎች ዘመናዊ ትምህርትና የፍርድ ቤት አሠራር የጥንቱን እያጠፋውና በነበር እያስቀረው ቢኾንም (በተለይ ከ1923ቱ ሕገ መንግሥት ከወጣና የዘመናዊ ፍ/ቤቶች ከተቋቋሙ በኋላ) በአንዳንድ ሥፍራዎች ‹የተጠየቅ ልጠየቅ› እና ‹የበልሃ ልበልሃ› ክርክሮች ልምድ እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ማሳያዎች አሉን፡፡ ለምሳሌ በመንዝ አካባቢ እስከ ቅርብ ጊዜ ይሠራበትና እዛፍ ሥር እየተሰበሰቡ መሟገት የተለመደ እንደነበር እና በጨዋታ በመከራከር የሚፎካከሩበት ሰዎች መኖራቸውንም በዚያ አካባቢ ለተወሰነ ጊዜ በማስተማር ላይ የቆየ ጓደኛዬ ነግሮኛል፡፡ የተጠየቅ ልጠየቅ ስልትን የመሠለ የሙግት ጥበብ እያለን፣ ለዚህም የተመዘገቡ የክርክር ማሳያዎች ሞልተውን፣ ከሥነ አመክንዮ ዕውቀት አንጻር (ተክለ ማርያም ፋንታዬ ‹ተጠየቅ› በሚል ርዕስ በ1953 ከጻፉት መጽሐፍ ውጭ) አለመመርመሩ ያስቆጫል፡፡ Read the rest of this entry »

Advertisements
 
 
%d bloggers like this: