RSS

Monthly Archives: October 2015

መኑ ውእቱ ዘፍልሱፍ- ፈላስፋ ማን ነው?

(በካሣሁን ዓለሙ)

‹ፍልስፍናን እማራለሁ› ብዬ ት/ቤት ብገባ፣ መምህሩ ‹ፍልስፍና ምንድን ናት?› ብሎ መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፤ ‹ካወቅኳትም ለምንስ ልማራት ሒሳብ ከፈልኩ?› አልኩኝ፤
‹ታዲያ ፍልስፍናን በገንዘብ ልተገዛ ነው እንዴ የመጣኸው?› ብሎ አፈጠጠብኝ፡፡
‹አይ! ገና ለማወቅ ነው የመጣሁት› አልኩት፡፡
በክፍል ውስጥ አብረን ከነበርነው ተማሪዎች መካከልም አንዱ ቀለብላባ ተማሪ ‹ፈላስፋ ማን ነው?› የሚል ጥያቄ አንሥቶ ገላገለኝ፡፡
መምህሩም ‹ፈላስፋ ምን እንደኾነ ንገረኝና የፍልስፍናን ምንነት አስረዳሃለሁ፤ ይባላል› አለን፡፡ ወይ ጣጣ ማብዛት! ‹ከየትኛው ነው የሚጀመር? ፍልስፍናን ከሚያወቀው ሰው ወይስ ከፍልስፍና ምንነት? ማንም ይፈላሰፋት ፍልስፍናን ካወቅናት አይበቃንም እንዴ? ደግሞስ ‹የፈላስፋን ምንነት ንገረኝ› ማለት ማንነቱን ከማወቅ ያነሰ፣ አሳቢውን ሰው ወደ ቁስነት የቀየረ አነጋገር አይኾንም?› የሚል ሐሳብ መጣብኝ፡፡ አላስችልም ስላለኝ ‹የፈላስፋው ማንነት ለምን እንደ ቁስ ተቆጥሮ በምንነት ይገለጻል?› አልኩት ለመምህሩ!
እሱም ጥያቄውን ወደ እኔ በማዞር ‹ሐሳቢ ሰው ምንነት የለውም ልትል ነው?› ብሎ አፋጠጠኝ፡፡
‹አይ! በቁስነቱ እየተከራከርን ጊዜ ከምናባክን በማንነቱ ተወያይተን የፍልስፍናን ምንነት ብንረዳ ይሻላል ብዬ ነው› አልኩት፡፡
እሱም በማስጠንቀቅ መልክ የዘመኑን አባባል ተጠቅሞ ‹ሲጀምር ጊዜ ከሌለህ ፍልስፍና ጋር አትድረስ፤ ሲቀጥል በፍልስፍና ትምህርት የማትስማማበትም ነገር ቢኾን ይነሳል፤ ሲቀጣጠል የፈላስፋውን ምንነት ሳታወቅ እንዴት ከማንነቱ ላይ ደረስክ? ምንነት የለውም ልትል ነው ወይስ በምንነቱ ላይ ጥያቄ አይነሳም፤ ታውቆ አልቋል ለማለት ፈልገህ ነው? ሲጧጧፍ በምንነትና በማንነት መካከል ያለው ልዩነት ገብቶሃል? ከገባህ አስረዳን፤ ካልገባህ ለማወቅ ጠይቅ እንጂ ሳታውቅ ለጥያቄው ያልተመለሰ መደምደሚያ አትስጥ!› እያለ ወረደብኝ፡፡ Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: