RSS

Monthly Archives: October 2014

ሙግት በእግዚአብሔር ጠባያት

(በካሣሁን ዓለሙ)

(ማስታወሻ፡- ከዚህ በፊት በሀልዎተ-እግዚአብሔር ዙሪያ በሻይ ቤት የተደረገ ሙግት በሚል ርዕስ ከአንድ ኢ-አማኝ ጋር ባደርግነው ውይይት ባለመግባባታችን ተለያይተን እንደነበር፤ ከዚያም  በኢ-ሜይል አድራሻዬ እግዚአብሔር በምን እንደሚታወቅ እንድጽፍለት ጠይቆኝ ጠባያተ-እግዚአብሔር በሚል ርዕስ የጻፍኩትን የእግዚአብሔር መታወቂያ ጠባያት እንደላኩለት ገልጬ ነበር፡፡ ከዚያም በኢ-ሜይል በእግዚአብሔር ጠባያት ዙሪያ ያደረግናቸውን ሙግቶች ለማቅረብ ቃል በገባሁት መሠረት በአንድነት ሰብስቤ አቅርቢያቸዋለሁ፡፡ ምንም እንኳን ጽሑፍ ረዥም እንደሆነ ቢሰማኝም፤ ከሚቆራረጥ አሳቡን ለማያያዝ በአንድ ላይ ቢሆን የተሻለ ስለመሰለኝ ነው፡፡ መልካም ንባብ!)

                እሱ፡-

ያ ወዳጄም የላኩለትን ጽሑፍ ካነበበ በኋላ በመልስ ደብዳቤው “የጻፍክልኝ የእግዚአብሔር መታወቂያ ጠባያት እርስ በርሳቸው የሚምታቱ (የሚጣረሱ) እና አሳማኝነት የሌላቸው ናቸው፡፡” አለኝ፡፡

                እኔ፡-

እኔም አለመኾናቸውን ለማስረዳት “‹የእግዚአብሔር መታወቂያ ጠባያትን ‹ትክክል ናቸው›  ብለን ካልተቀበልንማ አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለየትኛውም ነገር ማውራትና መናገርም አንችልም፡፡ ባለፈው እንደገለፅኩልህ ቋሚ የኾኑ ሕጎችን በመሠረታዊነት “ትክክል” ብሎ መቀበል በየትኛውም የዕውቀት ዘርፍ የተለመደ መነሻ ነው፡፡ እስቲ ቆይ ልጠይቅህ ቋሚ የኾኑ መሠረታዊ ህግጋት (postulate or axiom) የሌሉት የዕውቀት ዘርፍ አለ? አለ ለማለት የምትደፍር አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የትኛውም ዕውቀት በመሠረታዊ ሕግ (postulate) ላይ ይመሠረታልና፡፡ ከሌለ ደግሞ ለምን ታዲያ ከውቅያኖስ የሰፉትንና የጠለቁትን የእግዚአብሔር ጠባያት በዶግማነት “ትክክል ናቸው” በማለት አንቀበላቸውም?”  ብዬ የመልስ ጽሑፍ ላኩለት፡፡ Read the rest of this entry »

Advertisements
 
 
%d bloggers like this: