RSS

Monthly Archives: June 2014

በቀለ ተገኝ ስለፊደል

በቀለ ተገኝን ‹‹የምዕራባውያ ፍልስፍናና ሥልጣኔ ታሪክ ፩›› በሚል በ1985 ዓ.ም› ባሳተመው፣ በከፍተኛ የአማርኛ ቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ችሎታው የIMAG4856ተራቀቀበትን መጽሐፉን እየተገረመ ያነበበ ያውቀዋል፤ መጽሐፉን ያላነበበ ካለ ግን ትልቅ ቁም ነገር ቀርቶበታል፡፡ ለማንኛው እኔ እዚህ ስለ በቀለ ተገኝ ምንም ማለት አልፈለኩም፤ አልችልም፤ ሆኖም በመግቢያነት ከጻፈው ውስጥ ስለ ፊደላችን ያተተውን ብቻ (በተለይ ከገጽ 50-57 ካለው ውስጥ) መርጨ አቅርቤላሁ፡- በዚያው አጻጻፉንና በፊደላት መቆነጻጸር የነበረውን ቁጭት ማየት ይቻላል በሚል!

‹‹… ከፊደላቱ አቀራረፅ ጀምሮ እስከ ልሳነ ጥበቡ አወቃቀር፣ ከቅርቦቹም ይበልጥ፣ የጥንቶቹ አባቶቻችን በተራቀቀ ጥበብ አሣምረው የቀመሩልንን ብልሃት፣ ባርከውና መርቀው እንደአወረሱን አዙረን ማየት አቅቶናል፡፡ … እሊያ የጥንቱ ሊቃነ ልሳናችን መቸና እንዴት እንደሆነ ምንጩን እንዲነግሩን ከእኔ ለሚበልጡ፣ የታሪክ ሊቃውንት ፈንታውን ልተውላቸውና፤ ሊሆን እንደሚገባው፣ ከሕንፃው ነደቅታችን፣ ከሠዓሊያኑና ከአምሳለተ ቅርፁ ጠበብታን፣ ከቅኔ ዘረፋው፣ ከመዝሙረ ዳዊት ትርጓሜው፣ ከመኅሊዩ ዜማና፣ ከየዕውቀቱ የአእምሮ ምጥቀት በመጠቀም፣ በመመካከርና በመተጋገዝ ፊደላችንን ፈጥረውልን ነበር፡፡ … በዓለም ዙሪያ በተተከሉት ከማነ ምስባካት ሁሉ የሚደነቅልንን፣ የፊደል ገበታችንን፣ ተጨንቀው፣ ተጠበው ቀምረውልን ነበር፡፡ ከዚያ ወዲያም፣ ያን ረቂቅ የፊደላችንን ጥበብ፣ ከእናትና ልጁ፣ ከግእዝና ከአማርኛው ቋንቋዎቻችን ጋር፣ በተለይ በቤተክህነት ሊቃውንታችን ባለአደራነት፣ በጸጋ አውርሰውን፣ በክብር አልፈው ነበር፡፡ … Read the rest of this entry »

Advertisements
 

በሀልዎተ-እግዚአብሔር ዙሪያ በሻይ ቤት የተደረገ ሙግት

(በካሣሁን ዓለሙ)

አንድ ቀን ፒያሣ በሚገኝ አንድ ኬክ ቤት ውስጥ የሃይማኖት መጽሐፍ እያነበብኩ ቁጭ ባልኩበት አንድ ዕድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ የሚገኝ ወጣት አጠገቤ መጥቶ በመቀመጥ ጨዋታ ጀመረ፡፡ የማነበውንም መጽሐፍ ‹እስቲ ልየው› ብሎኝ አሳየሁት፡፡ ከመጽሐፉ ጋር ተያይዞ ባነሳቸው ጥያቄዎችና ነቀፌታዎች የተነሳ የሚከተለውን ክርክር ተጨቃጭቀን ተለያየን፡፡

ልጁ ክርክሩን የጀመረውም “አሁን ይህንን መጽሐፍ ብለህ ታነባለህ?” በሚል ነበር፡፡

እኔም ተናድጄ “ለምን አላነበውም መጽሐፍ አይደለም?” ብዬ በጥያቄ መለስኩለት፡፡

“ማለቴ በዚህ መጽሐፍ ጊዜህን ከምታባክን ለምን የተሻለ እውቀት ያላቸውን መጻሕፍት አታነብም?”

“ምን ዓይነት መጻሕፍት ናቸው የተሻለ ዕውቀት ያላቸው?”

“ለምሳሌ የፍልስፍና መጻሕፍትን አታነብም? ሰዎች ለጥቅማቸው ሲሉ እግዚአብሔር ፣ ሰይጣን፣ ኃጢያት፣ ጽድቅ፣ ኩነኔ ምናምን እያሉ የጻፉትን ተረታተረት ከምትለቃቅም?” አለኝ እያጣጣለ፡፡

“የፍልስፍና መጻሕፍት ኹሉ እግዚአብሔርን ይቃወማሉ እንዴ የሃይማኖት መጻሕፍትን እንደዚህ አምርረህ የምትቃወመው?”

“እንዴ! እግዚአብሔር እኮ! በድሮ ጊዜ ነገሥታትና ካህናት ለጥቅማቸው ሲሉ የፈጠሩት እንጂ የሌለ ነገር ነው፡፡ ይህንንም የፍልስፍና መጻሕፍት ብታነብ መረዳት ትችላለህ፡፡”

“እስቲ መጽሐፉን ተወውና አንተ እንደዚህ ለማለት የደረስከው የእግዚአብሔርን አለመኖር እንዴት ማወቅ ችለህ ነው?”

“እስከ ዛሬ ድረስ መኖሩን ማንም ሰው ሊያረጋግጥ አልቻለማ!” Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: