RSS

Monthly Archives: April 2014

የጥቁር አፈር ትሩፋት

( የኮተቤው የሻው ተሰማ)

ይኼ ያፈር አዋይ– ይኼ ያፈር ነዋይ…

ይኼ ያፈር ጌታ– ይኼ ያፈር ጎታ- ይኼ ያፈር ሲሳይ…

ይኼ ያፈር ወገን– ይኼ ያፈር ተገን …

ነፍስና ሥጋውን አፈር ያበጃጀው…

አክሊሉን ተክሊሉን አፈር ያቀዳጀው…

Read the rest of this entry »

Advertisements
 

እግዜርን ጠርቶ የለም ማለት መኖሩን በግማሽ መመሥከር

(በካሣሁን ዓለሙ)

በዚህ ዘመን እንደ ኢ-ኣማኝ ማስረጃ ሳይኖረው የሚቦርቅ ተጨቃጫቂ ዐላየሁም፡፡ አንድ ጊዜ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ‹ፍልስምና ፫› በሚለው መጽሐፉ ላይ አንዱን ኢ-አማኝ ነኝ ባይ ‹ስለ እግዚአብሔር አለመኖር ምን ማስረጃ አለህ?› ብሎ ሲጠይቀው ‹ኢ-አማኝ ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅበትም፤ አለ የሚል ነው ማቅረብ ያለበት› በማለት መልስ መስጠቱን አንብቢያለሁ፤ ይህች መከራከያም የተለመደች መሆኗን አውቃለሁ፡፡ ከሰሞኑም አንድ ጓደኛዬ ተመሣሣይ አስተያየት አቀረበልኝ፡- ‹‹እግዜር› አለ ብሎ የሚከራከር ሰው ‹አለ› ያለውን ነገር የማብራራት ሸክሙን የሚወስድ መሆኑ ነው፡፡ ቃል እና ሃሳብ ሆነው በማኅበረሰቡ ውስጥ የምናገኛቸውን ነገሮች ሁሉ ‹አሉ› የሚለው ሰው ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡››ይላል በሣጥኔ ውስጥ የተላከልኝ መከራከሪያ፡፡

እንደኔ እንደኔ ያለመሳረጃ መከራከር በተለይም ማስረጃ ያለውን ትቶ ማስረጃ እንደሌለው እያወቁ ለዚያ ጥብቅና ቆሞ እሞግታለሁ ማለት የእንቆቅልሽ ጨዋታ ይመስለኛል፡፡ የማይገባኝ ነገርም ኢ-አማንያን አቋም ይዘው የመከራከራቸው ነገር ነው፤ ጥብቅና መቆም እኮ! ለአመኑበት ነገር መመስከር ነው፡፡ አቋም ከሌላቸውና ‹መከራከር አንችልም› ካሉም መዘባረቅ የለባቸውም፤ እየተከራከሩና ‹እግዚአብሔር የለም› ለሚለው ለኢ-አማኝነት ጥብቅና ቆመው ከሆነ ‹ማስረጃ አቅርቡ› መባላቸውም አግባብ ነው፤ ሊያቀርቡ ይገባል፤ ያለበለዚያ ኢ-ኣማኝነት ትክክል ነው ብለው የሚከራከሩበት ምክንያት ምንድን ነው? ማስረጃ የለኝም ግን ትክክል ነኝ ብሎ ክርክር ምንድን ነው? ስለዚህ ‹እግዚአብሔር የለምን› አምነውበት እየተከራከሩ ስለሆነ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ምክንያታዊም መሆን አለባቸው፡፡ በሌላ በኩል የሚከራከሩት ማስረጃ ሳይኖራቸው ከሆነ ‹አንድትም ብጣቂ ማስረጃ ብትሆን ከተገኘች ለመቀበልና እምነታቸውን ለመቀየር ይገደዳሉ ማለት ነው፤ ምክንያቱም የሚከራከሩት ስለህልውና ነውና፡፡ Read the rest of this entry »

 

ፅርፈት ለማን ?ስለ አለቃ አያሌውና መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ መልስ አሠጣጥ


(ካሣሁን ዓለሙ)

ሰሞኑን አንድ በትምህርት ምክንያት ከተዋወቅኳቸው ትልቅ የቤተክርስቲን አባት ጋር ‹ሀልዎተ እግዚአብሔር› ስለሚለው መጽሐፌ እየተወያየን ነበር፡፡ በመሃል አንድ ጥያቄ አነሱብኝ፡- ‹የመጽሐፉን መታሰቢያ ለምን ለአለቃ አያሌውና ለመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ልታደርግ ቻልክ?› የሚል፡፡ ምክንያቴንም ነገርኳቸው፡- አንደኛ ኹለቱን አባቶች በመጽሐፎቻቸው ስለማውቃቸውና በሊቅነታቸውም ስለምደነቅ የቤተክርስቲያኔቱን ሊቃውንት ሊውክልሉኝ ይችላሉ ብዬ፤ ኹለተኛም እንደነዚህ ዓይነት ተመዋጋቾች እንደነበሩንና እንዳሉን ማሳያ ይኾናሉ በማለት፤ እንዲሁም እነሱ ለቤተክርስቲያንቱ ዶግማ፣ ተውፊትና ቀኖና በአደባባይ ግንባር ቀደም ኾነው በመከራከር አቃቢያን እምነት እንደኾኑት እኔም በመጽሐፌ ኢ-ኣማንያንን ለመሞገት ስለመኮርኩ ለማሳያነት ላስታውሳቸው ብዬ ነው አልኳቸው፡፡ ጥሩ ነው በርታ ብለው ከመከሩኝና ከመረቁኝ በኋላ ስለ ኹለቱ አባቶች አንዳንድ ነገሮችን አነሳን፡፡ Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: