RSS

Monthly Archives: March 2014

ልቃዊነት የዘመናችን ሃይማኖት

ካሣሁን ዓለሙ

ሃይማኖት በሥርዎ ቃሉ ማመንና መታመን የሚሉ ፅንሣተ-ሐሣብን የያዘ ቃል ነው፡፡ ማመን በአንድ ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲሆን መታመን ደግሞ ላመኑበት ነገር መታገልና መቆም ነው፡፡ ይህንን ይዘን ወደ ፍልስፍናው መከራከሪያ ስንገባ በዓለማችን የሚገኙ የሃይማኖት ይዘቶችን በሦስት ከፍለን ልንያቸው እንችላለን፡፡

1) በእግዚአብሔር ህልውነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Theist)

የእግዚአብሔር ህልውነትን በማመንና እሱን በመመሥከር እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ግኑኝነት የሚያደርግ በሥራው ፍፁም የሆነ አምላክ መሆኑን ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆች ከእነሱ በላይና ፍጹም ከኾነ ኃይል ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ፤ እሱም በመገለጥ ስለ ዐለማትና ፍጥረታት አፈጣጠር፣ ስለ ሰው ልጆች መፈጠርና ህልውና ነግሯቸዋል፤ ያኘጋግራቸዋል ብሎ ያምና፤ ለዚህም ጥብቅና ቆሞ ይመሠክራል፤ ይከራከራል፡፡

2) በእግዚአብሔር አለመኖር ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Atheist)

ይኸ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚክድና ለዚያም አቋም ጥብቅና የቆመ ሃይማኖት መሰል አስተምህሮ ነው፡፡ይህም ሃይማኖት የራሱ መታወቂያ አለው፡፡ በአንድ በኩል ሰይጣንን በግል እያመለከ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚቃወም ሲሆን በአብዛኛው በኢሉምናቲ የሚሥጢር ማኅበራት የሚቀነቀን ነው፤ ምሥጢራዊነቱም ያመዝናል፡፡ ስለዚህ በግልፅና በተቋማዊ አደረጃጀት የማይታወቅ ቢመስልም በአብዛኛው በሳይንስና በፍልስፍና አስተምህሮ ተወሽቆ እምነቱ ተቀባይነት አግኝቶ እንዲስፋፋ ጥረት ይደረግለታል፡፡ የዚህ ሃይማኖት አቀንቃኞች በዋናነትዝግመተ ለውጠኛችና ቁሳካላዊያን ናቸው፡፡ለምሳሌ እንደ ፈርደሪክ ኒቼ፣ ካርል ማርክስ፣ ሌኒን፣ ዳሪዊን፣ ሪቻርድ ዳውኪንስና መሰሎቻቸውን መጥቀስይ ቻላል፡፡

3) ‹አሊለም› (እግዚአብሔር አለ-የለም) ሃይማኖት (Agnostic)

የእዚህ ሃይማኖት መነሻው ልቃዊነት (Liberalism) ማሳለጫው ምንፍቅና (Skeptic) ተግባሩም ውል አልባነትና ግደለሽነት (indifference) ነው፡፡ የመከራከሪያ ስልቱም ዥዋዥዌ መጫወት ነው፡፡ Read the rest of this entry »

Advertisements
 

ግብረሶዶማዊነትን ለምን እንቃወማለን?

(ካሣሁን ዓለሙ)

አንዳንድ ጊዜ የግብረ ሰዶማዊነት የዚህን ያህል አሟጋች መሆኑን ሳይና በአለማቀፍ ተቋማት ድጋፍ አግኝቶ እንዲስፋፋ ሲደረግ ስመለከትና ስሰማ ይገርመኛል፤ ግርምቴ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም፤ ይልቁንም ግብረሰዶም ከሰው ልጆች ተፈጥሮ ውጭ የሆነ ተግባር መስሎ ስለሚታየኝና የሚሰጠው ጥቅም አልገለጽልህ ቢለኝ ነው፡፡ ስለዚህ የራሴን መሟገቻ ነጥቦች ላቅርብ ፈለግሁ ይህ ጽሑፍም በዚህ ዕይታ የተቃኘ ነው፡፡ መልካም ንባብ!

ለመሟገትም ‹ግብረሰዶማዊነት ተፈጥሮ የሚደግፈው ድርጊት ነው ወይ?› በሚል ጥያቄ መነሣት የግድ ይላል፤ መልሱም ‹ግብረሰዶማዊነት ተፈጥሯዊ ነው› የሚል ከሆነ ቢያስ መሠረታዊ መሥፈርትን ማሟላት ችሏል ማለት ይሆናል፤ ‹አይ! ግብረሰዶማዊነትማ ከሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ጠባያት ውጭ የሆነ ወይም ከስብዕና ተፈጥሮ ጋር የማይስማማ ድርጊት ነው› የሚለው ስምምነት ካገኘም ከተፈጥሯችን ውጭ ያሉ ድርጊቶችን የማከናወን መብት አለን ወይ? በድርጊቱስ የሚገኝ ኅብረተሰባዊ ጠቀሜታ ይኖራል? ጉዳትስ የለውም? ከሁለቱ ውጤቶችስ (ከጥቅሙና ጉዳቱ) የሚበልጠው የትኛው ይመስላል? የሚሉ ጥያቄዎች ፊት ለፊታችን መጥተው ያፈጣሉ፡፡ በእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ብንስማማ እነኳን ሌሎች ጥያቆዎችም መምጣታቸው አይቀርም፤ ለምሳሌ የሞራል ጥያቄዎች፣ የማኅበረሰብ ደኅንነት፣ የመንፈሳዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጉዳይና የመልካምነት ጉዳይ በቀላሉ የሚገፉ ወይም የሚተው አይሆኑም፡፡ Read the rest of this entry »

 

የአድዋ ማስታወሻ

1. ጎራው

ጎራው! አይደለም ወይ! ወኔ መቀስቃሻው ለአበሽ ጀግንነቱ፣

በጎራ አይደለም ወይ ጥንትስ ኢትዮጵያውያን የሠለጠንቱ፣

አድዋም ጎራ ነው ኢትዮጵያዊ ወኔ የከተመበቱ፣ Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: