RSS

Monthly Archives: October 2012

እውን ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና የለም? (2)

(ባለፈው ስለ ኢትዮጵያ ፍልስፍና መኖርና ‹ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና የለም› የሚሉ ተከራካሪዎች የሚቀርቡትን መከራከሪያ በጥቅል በማቅረብ ጽሑፉ አቁሞ ነበር፤ ከዚያ የቀጠለው ተከታይ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1.  የመተቻቸትና የመወያየት ባህል አለመኖር

  1.   በአፍሪካ ውስጥ በፍልስፍና ዙሪያ በሀገሮች መካከል የሚደረግ የመተቻቸትና የመከራከር ባህል የለም፡፡
  2. የመተቻትና የመከራከር ባህል በሌለበትም ፍልስፍና አይኖርም፡፡
  3. ኢትዮጵያም ውስጥ ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡
  4. ስለሆነም የፍልስፍና ባህል በአፍሪካ ውስጥም ሆነ በኢትዮጵያ የለም፡፡

ይህ ክርክር ‹ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና የለም› የሚሉ ምሁራን አመክንዮአዊ አቀራረብን የተከተለ አንደኛው መከራከሪያቸው ነው፡፡ እውን ግን ይህ አሳማኝ ነው? አሳማኝነት ያለው ለመሆን የአቀራረብ ትክክልነት ብቻ ሳይሆን ይዘቱም እውነት መሆን ይኖርበታል፡፡ እውን የቀረበው ትክክልና እውነት ነው ወይ? ብሎ መፈተሸ ግድ ነው፡፡ በአጭሩ እውን የመተቻቸትና የክርክር ባህል የለንም ወይ? የትችትና የክርክር ባህል ያለን ከሆንን ‹ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና የለም› የተባለበት ምክንያት ስህተት ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ባህል የሌለን ከሆንም ፍልስፍና ለመኖር የትችት ባህል መኖር ዋሳኙ መሆኑ ወይም አለመሆኑ መመዘን አለበት፡፡ Read the rest of this entry »

Advertisements
 

እውን ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና የለም?

አንድ ጊዜ ፍቅሬ ቶሎሳ(ዶ/ር) የተባሉ የጦቢያ ምሁር Ethiopian needs spiritual leaders በሚል ርዕስ (The Eye on Ethiopia and The Horn of Africa vol. XXXV NO. 126 nevember 2006) ባወጡት ጽሑፍ ላይ:

‹ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህል፣ ፍልስፍና፣ ሥነ ተረትና ሥነ ጽሑፍ ብዙም እውቀት የሌላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ መሪዎችና አብዮተኞች የምዕራባውያን ታሪክ፣ ባህል፣ ፍልስፍና እና ሥነ ጽሑፍ ሊቆች ነበሩ፡፡ ለዚህም ይህ ጥሩ ማሳያ የሚሆን ምሳሌ ይሆናል፡፡ ሁለት ኢትዮጵያን ሊቆች የጦፈ ጨዋታ ይዘዋል፤ በመሃል በኢትዮጳያ ታሪክ ዙሪያ ሰፊ ዕውቀት ያለው አንደኛው በምዕራባውያን ትምህርት ዶክተር የሆነውን ጓደኛውን ስለ ኢትዮጵያ ፍልስፍና ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ የምዕራባዊያን ፍልስፍና ሊቅ የሆነው ዶክተር ግን መልሶ በሚያስደንቅ ሁኔታ ‹ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ፍልስፍና አላት?› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ የታሪክ ምሁሩም ‹በክላውድ ሰምናር የተጻፉት እነዚህ ሁሉ መጻሕፍት ምንድናቸው? ስለ ኢትዮጵያ ፍልስፍና አይደለም እንደ የሚናገሩት? ደግሞስ ኢትዮጵያ ፍልስፍና የላትም ብለህ ካመንክ  አንተ የፍልስፍና ምሁር አይደለህም? ፍልስፍና እንዲኖራ ለምን አንተ ራስህ የፍልስፍና መጽሐፍ አታዘጋጅም?…› ብሎ አፋጠጠው፡፡ ነገሩ ግልፅ ነው፡፡ የፍልስፍናው ምሁር ስለ ጀርመን ፈላስፎች ሄግልና ማርክስ በጥልቀት ያውቃል እንደ እነ ዘርዓ ያዕቆብና ወልደሕይወት ስላሉት ኢትዮጵያውያን ፈላስፎች መኖር ግን የሚያወቀው ጉዳይ ላይኖር ይችላል፡፡ይህም አንድ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ሥልጣኔ ሳወራ ይህንን የማያውቅ አንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ‹የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ደግሞ ምንድን ነው?› ብሎ የጠየቀኝን መቼም መርሳት አልችልም፡፡ ይህ ምሁር ግን ከላይ እንዳለው የፍልስፍና ምሁር ስለ አውሮፓውያን ስልጣኔ በቂ ዕውቀት ያለው የሚባል ነበር፡፡ እንደሱ ከሆነ በእውነቱ  ኢትዮጵያ ነበራት ተብሎ ሊወራ የሚችል ምንም ዓይነት ሥልጣኔ አልነበራትም በሚል እምነት ተሞልቷል፤ ሥልጣኔ ያለውና የፈለቀው ከምዕራብ ብቻ ነው፤ ስለዚህ የትኛውም ሥልጣኔ የምዕራባዊያን ሥልጣኔ ላይ ጥገኛ ነው በማለት ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡…›  በማለት ያስቀመጡት ለዚህ ርዕስ ጥሩ ማሳያ መግቢያ ይሆነናል፡፡ Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: