RSS

ቅኔ የፍልስፍና ላዕላይ ጥበብ

(በካሣሁን ዓለሙ)

መስከረም 13 ቀን 2010 ዓ.ም በወጣዉ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ብሩህ ዓለምነህ የተባለ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር እና ‹የኢትዮጵያ ፍልስፍና› የሚል መጽሐፍ ደራሲ ‹ለመሆኑ ቅኔ ፍልስፍና መሆን ይችላል?› በሚል ርዕስ በቅኔ ፍልስፍናነት ላይ ትችት አቅርቧል፡፡  በእውነቱ ያነሳው ሐሳብ ስለ ፍልስፍና ጥሩ አገራዊ የክርክር መነሳሳትና ዕይታን የሚፈጥር ስለሆነ የበለጠ ትጋትንና የዕውቀት ብልፅግናን ያድልልን እላለሁ፡፡

እኔም በተነሳው ሐሳብ ላይ የራሴ የጥናት ጅማሮ ስላለኝ ምልከታየን ላከፍል ፈለኩ፡፡ ይሁንና በጽሑፌ የብሩህን መጽሐፍ ለመተቸት አልተነሣሁም፤ የኢትዮጵያ ፍልስፍናን ይዘትም ማሳየት ማጠንጠኛዬ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ቅኔን ከደረጃዋ አውርደን በአመድ ላይ እንዳናከባልላት ከፍተዋን በመጠኑ ለማሳየትና ለመሞገት ነው፡- አነሣሤ፡፡ ካስፈለገ የብሩህ መጽሐፍን ለመሔስና የኢትዮጵያን ፍልስፍና ይዘት ለማሳየት በሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፡፡ Read the rest of this entry »

Advertisements
 
 

የዕውቀት መፍለቂያው ልቦና፣ ሕሊና ወይስ የስሜት ሕዋሳት?

‹ልቦናን› ስናነሣ ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ ‹የዕውቀት መፍለቂያው ምንድን ነው?› የሚለው ጥያቄ ነዋ! የዕውቀት ምንጩን ማወቅ ደግሞ ጭንቅ ነው፤ ምክንያቱም የዕውቀት የመገኛ ምንጩና አገኛኘቱ በትክክል መታወቅ ከተቻለ የማይታወቅ ነገር አይኖርም፡፡ የማይታወቅ ነገር ከሌለም ፍጹማዊ ዕውቀትን ገንዘብ ማድረግ ይቻላል፡፡ ፍጹማዊ ዕውቀትን ገንዘብ ማድረግ የሚችለው ግን ልዕለ ኃያል የኾነው እግዚአብሔር እንጂ በችሮታ የሚያገኘውን ዕውቀት በቅደም ተከተል፣ በመርሳትና በማስታወስ እየመረጠ የሚያገናዝበው የሰው ልጅ አይደለም፡፡ ለብዙ ሰው ዕውቀት በምንጩ የተወሳሰበ ስለሚመስለው በአግባቡ ለይቶ ለማሰብና የተሻለ አስተሳሰብን ገንዘብ ለማድረግ ይቸገራል፡፡ በሌላ በኩል የሚያውቀው ዕውቀት የተደበላለቀበት ሰው ምንጩን ካላወቀ ‹ከየትና እንዴት› የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይቸገራል፤ ‹ከየት› የመረጃ ምንጭ፣ ‹እንዴት› ደግሞ የማወቂያ ዘዴ (ስልት) ነውና፡፡ ይህ ከኾነም ማንኛውም ተመራማሪ ቢያንስ የተቻለውን ያህል የዕውቀቱን አገኛኘት መለየት ይገባዋል፡፡ Read the rest of this entry »

 

የሸቃዩ ትዝብት

(በካሣሁን ዓለሙ)

ሽቀላ የጀመርኩት መጽሔቶችን ጮኾ በመሸጥ ነው፤ የመጽሔት ሽቀላን ታሪክ አረሳውም፤ ብዙ ነገሮችንም ታዝቤበታለሁ፤ ምሁራን የሚያነቡትንም ለማወቅ ችያለሁ (ምሁራን የሚያውቁት በማንበብ አይደል!)፡፡ መጽሔት ስሸቅልም ቶሎ  ቶሎ ሸጬ ትርፋማ ለመኾንም የሚያስችለኝን  የማሻሻጫ ዕውቀት አዳብሬያለሁ፤ ሳነብ ግን ስልትን እጠቀማለሁ እንጂ ዝም ብዬ አልሸመድድም ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ ከመጽሔቱ ላይ የምፈልገው እውቀት መጽሔቱን ለማሻሻጫነት እንጂ ከዚያ ያለፈው አይመለከተኝም፡፡

ዕወቀትም የማሻሻጫ መሣሪያ እንደኾነም ይሰማኛል፡፡ ለምሳሌ የአንድን መጽሔት ርዕስ ‹ጥሩ አድርጎ በካርቶን፣ በተመረጡ ቃላት ወይም የቃላቱን አጻጻፍ በማሳመርና በማጉላት ማስጮህ› የሚጠቅመው ያየው ሰው እንዳያልፈው ለማድረግ ነው፤ ስለዚህ የመጽሔቱን (ወይም የጋዛጣም ሊኾን  ይችላል) ርእስ ማስጮህ ዕወቀት ነው፤ የጩኸቱም ግብ በብዛት እንዲሸጥ ለማድረግ ነው፡፡ ሌላም ምሳሌ ላንሳ አንድ መጽሔት አዘጋጅ የተሻለ ዕውቀት ያለቸውን ሰዎች በመጠየቅ ወይም በማጻፍ ካካተተ በብዛት ይሸጥለታል (ለምሳሌ ጦቢያ የተባለው መጽሔት ዋና ማሻሻጫ ፀጋዬ ገብረመድኅን (ሎሬቱም ኾነ አርአያው) እንደነበር አስታውሳለሁ)፤ ይህም ማለት የዐዋቂው ሰዉየ ዕውቀት ለማሻሻጨነት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ማለት ነው፡፡ ደግሞስ ድለላ (የገበያ አፈላላጊም ይባላል)፣ የማስታወቂያ ሥራ የመሳሰሉ ሥራዎች ድግሪ የተመርቁ ሰዎች የሚሠማሩባቸው አይደሉም እንዴ! ከእነዚህ የበለጠ የዕውቀት አሻሻጭነት ምሳሌ ሌላ ምን ያስፈልጋል? ስለዚህ እኔም የመጽሔትን ዕውቀት ለማሻሻጫነት መጠቀሜ ትክክለኛ ዐዋቂነት ነው፡፡ ከማይሠራበት ብዙ ዕውቀትም የኔ የማሻሻጫ ዕውቀት ሳይሻል አይቀርም፡፡ Read the rest of this entry »

 

ስለ መሪ ራስ አማን በላይ

በ1997 ዓ.ም ገደማ ከአማን በላይ መተዋወቅ እንደጀመርን በየጊዜው እየተደዋወልን ለረጅም ሰዓቶች በስልክ እናወራ ነበር። ለሀገሩ ሰው ያለውን ሁሉ ዕውቀት የማካፈል ምኞት ስለነበረው አብዛኛውን ጊዜ የሚናገረው እርሱ ነው። እጅግ ሰፊ ትንታኔና ሐተታ ማቅረብ ይችል ነበር።

via መሪራስ አማን በላይ (፲፱፻፵፪-፳፻፱) — ሰምና ወርቅ

 

ፍልስፍና-ቅኔ (ጥበበ-ቅኔ) ፪

(በከሣሁን ዓለሙ)

መጀመሪያ ይህንን link ማንበብ ጠቃሚ ነው፡፡

ቅኔ ለምን ከኹሉም በላይ የሚታይ ዕዉቀት ኾነ? ነዉ ሊቃውንቱ ከዚያም ባለፈ እንደእነ ከበደ ሚካኤልና መንግሥቱ ለማ ዓይነት ምሁራን ቅኔን የሚያገኑት ሌሎችን ዕዉቀቶች ካለመረዳት ይኾን? እንደ እኔ ግንዛቤ ሌሎቹን ካለመረዳት አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም የቅኔ ድንቅነትን ስለተገነዘቡ ይመስለኛል፤ ዋና ጉዳያችን ግን የእነሱ ልቅና ሳይኾን የቅኔ ዕውቀት ምጥቀት፣ ስፉህነትና መሠረታዊነት መመርመር ነው፡፡

ከኹሉም በፊት ከዚህ በፊት እንደጠቀስነው በሀገራችን ሊቃዉንት ቅኔ የተለየና የተከበረ ዕዉቀት መኾኑን እናዉቃለን፤ ይህ ከኾነ ‹ቅኔ እንዴት የተለየና የተከበረ ዕዉቀት ሊኾን ቻለ? የቅኔ ልዩ ፍልስፍና ምንድን ነዉ?› በሚል ጥያቄ ተነሥተን እንመርምር፡፡ ‹ቅኔ ሆይ! ፍልስፍናዬ ምንድን ነዉ ትላለህ? ነዉ ለፍልስፍናም ወላጁ እኔ ነኝ ባይ ነህ?›

በእነዚህ ጥያቄዎች በመመሥረት የቅኔን ዕሳቤና ምጥቀት ከተለምዷዊ ዕይታ መጠቅ አድርገን ማየት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም ከመጀመሪያዉ ጥያቄ በመነሣት እየፈተሸን እንሂድ፡፡ የሀገራችንን የግዕዝ ቅኔ ፍልስፍና ማርዬ ይግዛዉ እንዲህ በማለት ገልጾታል፡፡ Read the rest of this entry »

 

ጥበበ-ቅኔ (የቅኔ ፍልስፍና)-፩

(በካሣሁን ዓለሙ)

‹ዕዉቀት ቢወዳደር ድርሰት ቢፎካከር፣

ሁልጊዜ ቅኔ ናት የድርሰቱ ጀምበር፡፡›

ከበደ ሚካኤል

መዳረሻ

የቅኔን ምንነት ተረድቶ ለማስረዳት የቅኔዉ ባለቤት መኾንን ይጠይቃል፤ ችግሩ አልጠግብ ባይ ወይም ችግረኛ ‹የማትሞላ ዓለም› እንደሚለዉ የቅኔን ፍልስፍና ለማስረዳት የዕዉቀት ሕጸጽ ስላለ አንዱ ሲሟላ ሌላዉ እየጎደለ ቅኔም በሰፊዉና በአግባቡ ሳይጠና ይቀራል፡፡ በአንጋረ ፈላስፋ አንድ ፈላስፋ ‹ጊዜ፣ ዕድሜ፣ ቦታ፣ ፈቃድ፣ ችሎታና ስምምነት እነዚህ ፮ (6) ነገሮች ከተረዳዱ ሥራ ኹሉ ይፈጸማል› እንዳለዉ የተሟላ መልስ በማግኘት የቅኔን ምንነት በአግባቡና በቅኔነቱ ለመግለጽም የሰዋሰዉ ሥርዓትን (እርባ ቅምርንና አግባብን) እና የቅኔ ስልትና ዓይነትን ጠንቅቆ ከማወቅም በተጨማሪ የፍልስፍና ዕዉቀትን ይዘትና ቅርጽ በአግባቡ መረዳት ያስፍልጋል፡፡ ይኹንና በዐቅም ዉስንነት ሰበብ ያሰቡትን ሐሳብ ሳይገልጹ ዝም ከማለትና የአስፈላጊ ነገሮችን መሟላት ከመጠበቅ የተገነዘብኩ የመሰለኝን ሞክሬ የቀረዉን ሊቃዉንቱ በቁጭት እንዲያሟሉትና እንዲተቹት ወይም እንዲያሻሽሉት መተዉ የተሻለ መስሎ ይሰማኛልና በግሌ ይህን ስሜቴንና የተገነዘብኩ የመሰለኝ  ሐሣብ ላካፍል ፈለግሁ፡፡ Read the rest of this entry »

 

የጥበብ መጀመሪያ መደነቅ ወይስ እግዚአብሔርን መፍራት?

(በካሣሁን ዓለሙ)

የሀገራችን የጥበብ አረዳድ ‹እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው› በሚለው በጠቢቡ ሰለሞን መርህ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሶቅራጥስ ደግሞ ‹መፈላሰፍ በመደነቅ ትጀመራለች› በማለት ገልጽዋል፡፡ እነዚህ የጥበብ መሠረታዊ መርሆች የሚጣረሱና የማይስማሙ ይመስላሉ፡- ‹‹ፈሪ› ነው፤ ‹ተደናቂ› ጥበበኛ!?› በሚል ጥያቄ ተነሥቶ የጥበብ መሠረቱ ‹መደነቅ› ነው ወይስ ‹መፍራት› በሚል ማጠንጠኛ ላይ ይሽከረከራል፡፡ ‹ገለጻዎቹስ በምሥጢር የሚገናዘቡ ናቸው የሚጻረሩ?› የሚል ጥያቄም አብሮ አለ፡፡

ካስተዋልነው ግን የሶቅራጥስ ገለጻ ከሰው ልጅ ዕውቀትን መሻትና ምርምር ናፋቂነት አንጻር የተቃኘ ሲኾን የሰለሞን ደግሞ ከሰፊውና ከምጡቁ ከእግዚአብሔር ማንነትና ከሰው ጋር ከሚያደርገው መስተጋብር ጋር ይገናዘባል፡፡ ችግር የሚፈጠረው በአንድኛ ዕይታ ዙሪያ ብቻ ተሸብቦ በመገተር እንጂ (በተለይ ሶቅራጥስኛ ላይ ተገትሮ መቅረት ልማድ ኾኗል) ኹለቱም በዕይታ አንግላቸው ቢለያዩም በአስተውሎታቸው የሚገናዘቡ ይመስላሉ፡፡ Read the rest of this entry »

 
 
%d bloggers like this: